top of page
new conceptual design.png

የቤተ ክርስቲያን ማስፋፊያ ፕሮጀክት፦ ለወደፊት ራዕያችን

የደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል የኢ.ኦ.ተ. ቤተ ክርስቲያን ተገልጋይ የምዕመናን  ቁጥር እያደገ በመምጣቱ በተቻለ መጠን የመቅደሳችንንም ይዞታ  የማስፋት አስፈላጊነቱን ካሁን ቀደም  በምስል በማስደገፍ ለምዕመናን ባቀረብንላችሁ የዕርዳታ ጥሪ መሰረት የሁላችሁንም ድጋፍና ከዚያም በላይ ለመጀመሪያው ዙር የሃያ ሺህ ዶላር ዕርዳታችሁን ማሰባሰባችን የታወቀ ነው::

 

በዚህ መሰረት የግንባታ ሥራውን ደረጃ በደረጃ ለማስጀመርና ሰፊ የማስቀደሻ ቦታችንን በቶሎ ለማግኘት ዛሬም እንደ ትላንቱ  የሁላችሁንም የገንዘብ ልገሳና የጸሎት ዕርዳታችሁን በእጅጉ እንሻለን:: በመሆኑም ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች 

የበጎ ሥጦታችሁን እጆች ትዘረጉልን ዘንድ ቤተክርስቲያናችሁ ጥሪዋን ታሰማለች::

 

ይህንን በማድረጋችሁም ከእግዚአብሔር ሰላምና ጤንነትን ፣ ከእመቤታችንም ረድኤትና በረከትን ፣ ከቅዱስ ገብርኤልም ጥበቃውንና ታዳጊነቱን ታተርፉበታላችሁ:: በሥራችን ሁሉ እግዚአብሔር ይጨመርበት

 

የደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ሰበካ ጉባኤ::

Target for Phase 2 = $15,000

© 2025

bottom of page